በአቡዳቢ ምስካየ ሕዙናን መድኀኔ ዓለም ወአቡነ ተክለ ሃይማኖት ግዳም የሚያገለግሉ ካህናት አብዛኞቹ ተቀጥረው ደመወዝ እየተከፈላቸው የሚያገለግሉ ሳይሆኑ በውጭ ሌላ ሥራ እየሠሩ፣ እንዲሁም በሀገሪቱ መንግሥት የትምህርት ዕድል አግኝተው፣ በዚህም ሀገር ተወልደው አድገው እየተማሩ በትርፍ ሰዓታቸው በበጎ ፈቃድ የሚያገለግሉ ሲሆን አገልግሎታቸውም በማሕሌት፣ በኪዳን፣ በቅዳሴ፣ ቀሳውስቱ በመምህረ ንስሓነት እና በመሳሰሉት ነው። በዚህ ሰዓት አጠቃላይ በገዳሙ መንፈሳዊ አገልግሎት እየሰጡ ያሉ ካህናት ብዛታቸው 25 ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ ዘጠኙ ቀሳውስት ሲሆኑ ዐሥራ ስድስቱ ደግሞ ዲያቆናት ናቸው።
ማኅበረ ካህናት ዘአቡዳቢ (CLERGY – ABU DHABI)