ሰበካ ጉባኤ (PARISH COUNCIL)
ሰበካ ጉባኤ እና ዓላማው
ሰበካ ጉባኤ: ቅድስት ቤተክርስቲያን ዘመናዊ መዋቅር ያላት ሆና እንድትተዳደር በተደነገገው ህግ ቃለ ዓዋዲ መመስረት ጋር አብሮ የተጀመረ መንፈሳዊ ጉባኤ ነው፡፡ ሰበካ ጉባኤ በቃለ አዋዲ አንቀፅ 5 መሰረት የሚከተሉት አለማዎች አሉት፡፡
- ቅድስት ቤተክርስቲያንን ለመጠበቅና አገልግሎቷም የተሟላ እንዲሆን ለማድረግ፤
- የቤተክርስቲያንን አገልጋዮች ሐዋርያዊ ተግባር ለማደራጀትና እንደዚሁም ችሎታቸውንና ኑሮአቸውን ለማሻሻል፤
- ምዕመናንን ለማብዛት እንደዚሁም በመንፈሳዊ ዕውቀት ጎልምሰው በምግባርና በሃይማኖት ጸንተው በክርስቲያናዊ ህይወት እንዲኖሩ ለማድረግ፤
- የቤተ ክርስቲያንን አስተዳደር ለማሻሻልና በማናቸውም ጉዳይ ራሷን ለማስቻል ነው፡፡
ከዚህ በተጨማሪ በቃለ ዓወዲው አንቀጽ 6 ላይ ሰበካ ጉባኤው የሚከተሉትን ተግባራት እንደሚያከናውን ተደንግጎ ይገኛል፡፡
- የእግዚአብሔርን ወንጌል መንግስት ለመስበክና ትምህርቱንም ለማስፋፋት፤
- መንፈሳዊና ዘመናዊ ትምህርት ቤትን ለማቋቋምና ለማደራጅት፤
- መንፈሳዊና ማህበራዊ አገልግሎትን ለምዕመናን ሁሉ ለማደረስ፤
- ሰንበት ትምህርት ቤትን ለማቋቋምና ለማጠናክር፤
- የቤተ ክርስቲያን አገልግሎትን ለምዕመናን ሁሉ ለማድረስ፤
- ለቤተክርስቲያን አገልግሎት የሚያስፈልጉትን ሁሉ ለማሟላት፤
- የቤተክርስቲያን አስተዳደርና አገልግሎት በቅዱሳት መጻህፍት መሰረት በህግና በሥነ-ሥርዓት ለመምራት፤
- ቤተ ክርስቲያንን በሀብትና በንብረት በኩል ራሷን ለማስቻል፤
- የቤተክርስቲያን ሀብትና ንብረት እዳይባክን፣ እየተመዘገበ እንዲጠበቅ፣ እንዲለማና እንዲያድግ ለማድረግ፤
- ህገ ቤተክርስቲያን በሚፈቅደው መሰረት ከበላይ የሚሰጡትን ህግጋት፣ ደንቦች፣ መመሪዎች፣ ትዕዛዞችና ውሳኔዎች ለመፍጸምና ለማስፈጸም፤
- በቅርብም ሆነ በሩቅ የሚገኙ ሰበካ መንፈሳውያን ጉባኤያት በማናቸውም ጉዳይ እርስ በእርሳቸው ተባብረውና ተረዳድተው እንዲሰሩ የተቻለውን ሁሉ ለማድረግ፣
- ልዩ ልዩ የምግባረ ሰናይ ድርጅቶችን ለማቋቋምና አገልግሎታቸውን ለማሟላት፣
- የህንፃ ሥራ፣ እድሳት፣ ጥገናና የመሳሰሉት ሥራዎች ሁሉ ወቅቱን ጠብቀው የሚፈጸሙበት እቅድና መርሃ ግብር ማዘጋጀት በተግባር መዋላቸውንም ለመቆጣጠር፤
- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታዮችን ብዛት ፣የሰበካውን ገንዘብና ንብረት ገቢና ወጪ የመሳሰሉትንም እስታቲስቲካዊ መረጃዎችን በወቅቱ እየመዘገቡ በሪፖርት እንዲገለጽ ለማድረግ፤
- በዚህ ቃለ ዓዋዲ መሰረት ማናቸውንም ቤተ ክርስቲያንን የሚመለከት ጉዳይ ለመፈጸምና ለማስፈጸም፤
- በዚህ አንቀጽ ከንዑስ አንቀጽ 4 እስከ 14 የተዘረዘሩትን ተግባሮች በቅድሚያ እያጠና ተገቢውን ለማድረግና አስፈላጊም ሆኖ ሲገኝ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ግለሰቦችና ድርጅቶች ጋር እየተነጋገረ ለማስፈጸም፡፡
Brief Summary of Duties and Responsibilities of the Parish Council
The Parish Council, serves as the executive body, manages the church’s spiritual, administrative, financial, and developmental activities. It safeguards the faith, traditions, and heritage of the Church, oversees clergy and youth programs, ensures transparent financial management, supervises construction projects, enforces discipline, and reports to the diocesan office. It also represents the parish in legal and administrative matters and coordinates with higher church bodies to fulfill the Church’s mission.
የሰበካ ጉባኤ አባላት (PARISH COUNCIL MEMBERS)
መርስዔ ሐዘን ቆሞስ አባ በአማን ግሩም (ዶ/ር)
ዋና ሰብሳቢ
ዶ/ር አብዮት ምንዳዬ
ምክትል ሰብሳቢ
ኢ/ር ኀይሉ መንግስቱ
ዋና ጸሓፊ
አቶ እንዳለው መኰንን
ቁጥጥር ክፍል
አቶ አምሳሉ አየለ
ሒሳብ ክፍል
አቶ ዮናስ መንገሻ
ም/ሒሳብ ክፍል
አቶ በኀይሉ ተሾመ
ገንዘብ ያዥ
አቶ ጥላሁን ከፈለኝ
ንብረት ክፍል
አቶ ጋሻው አበበ
ጠቅላላ አገልግሎት
ሊ/ዲ ግርማ ተመስገን
የማህበረ ካህናት ተወካይ
አቶ ጸጋዬ ፈቃዱ
የሰ/ት/ቤት ተወካይ
